top of page

ህዳር 9፣2017 - በመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የቦርድ አባላት የሚመረጡበት መስፈርት ተደርጎ የተቀመጠው ጥያቄ አስነሳ፡፡

በመገናኛ ብዙሃን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ የቦርድ አባላት የሚመረጡበት መስፈርት ተደርጎ የተቀመጠው ጥያቄ አስነሳ፡፡


ጥያቄው የቀረበው #የመገናኛ_ብዙሃን_ማሻሻያ_ረቂቅ_አዋጅ ላይ ከሚመለከታቸው ተቋማትና ባለድርሻዎች ጋር ዛሬ ውይይት እየተደረገበት ባለበት ወቅት ነው፡፡


በቀድሞ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ፤ የቦርድ አባላት የሚመረጡበት መስፈርት #የፖለቲካ_ፓርቲ_አባል ያልሆነ፣ ተቀጣሪ ያልሆነ የሚለው ለምን እንደተሰረዘ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ጠይቋል፡፡


ቋሚ ኮሚቴው በቀድሞ አዋጅ የፓርቲ አባል ያልሆነ ወይም ተቀጣሪ የሚለው ተሰርዞ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ከሆነ የፓርቲ ውግንና አይኖረውም ወይ? በሚዲያዎችም ሆነ በህብረተሰቡ ዘንድ ታማኝነት አያሳጣውም ወይ? የሚል ጥያቄ ተጠይቋል፡፡

በተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ የፖለቲካ ፓርቲ አባል የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የቦርድ አባል እንዲሆን የሚፈቅድ ነው፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እንድሪስ ይህ ጥያቄ የመጣው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን ካለማመንና በጥርጣሬ ከመመልከት ነው ብለዋል፡፡


ባለስልጣን መ/ቤቱ በአዋጅ የተቋቋመሆኖ ሳለ ይህን መሰል ጥርጣሬ ከየት እንደመጣ ሊገባን አልቻለም ብለዋል፡፡


መስሪያ ቤቱ በደንብ ነፃ እንዲሆን የፖለቲካ መብታቸውን በመገደብ የፖለቲካ አባል መሆን እንዳይችሉ፣ #የሃይማኖት አደረጃጀት እንዳይፈጥሩ ግዴታ የተጣለባቸው ሰራተኞች ያሉበት ነው ብለዋል ባለስልጣኑ፡፡


መ/ቤቱን እንደ ሌላ አካል አድርጎ ማየት እንደማያስፈልግ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡


ተሻሽሎ ዛሬ ውይይት እየተደረገበት ያለው ረቂቅ አዋጅ 10 ንዑስ አንቀፆች ተሰርዘው ዳግም በሌላ የተተኩበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡


ይህንን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ በርካታ #የሲቪል_ማህበረሰብ_ድርጅቶች የተቃውሞ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል፡፡


በቀረበው የማሻሻያ አዋጅ ውስጥ የአዋጅ ቁጥር 1238/2013 አምስት ንዑስ አንቀፆች በጠቅላላ ተሰርዘዋል የተባለ ሲሆን 10 ንዑሳን አንቀፆች ደግሞ ተሰርዘው እንደገና በሌላ ተተክተዋል ተብሏል፡፡


ይህን ለምን እንደሆነ ጥያቄ አስነስቷል፣ ውይይትም እየተደረገበት ነው፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Commenti


bottom of page