top of page

ሐምሌ 10፣2015 - ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬይን የክላስተር ቦምብ ለውጊያ እንዳታውል በብርቱ ማስጠንቀቃቸው ተሰማ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jul 17, 2023
  • 1 min read

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬይን የክላስተር ቦምብ ለውጊያ እንዳታውል በብርቱ ማስጠንቀቃቸው ተሰማ፡፡


ዩክሬይን ካለፈው ሳምንት አጋማሽ አንስቶ ከአሜሪካ ክላስተር ቦምቦችን መረከብ መጀመሯን ዘ ቴሌግራፍ ፅፏል፡፡


የዩክሬይን ሹሞች በሩሲያ የተነጠቅናቸውን ግዛቶች ለማስመለስ ክላስተር ቦምብ እንጠቀማለን ብለዋል በግላጭ፡፡


የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ዩክሬይን የክላስተር ቦምቦቹን ለውጊያ ካዋለች እኛም በአፀፋው ቦምቦቹን ከመጠቀም ወደ ኋላ አንልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡


አገራቸው ከፍተኛ የክላስተር ቦምቦች ክምችት እንዳላትም መዘንጋት እንደማይገባ ፑቲን አስታውሰዋል፡፡


ክላስተር ዋነኛው ቦምብ ሲፈነዳ በውስጡ የታመቁ ሌሎች ተፈነጣጣሪ ቦምቦችን በሰፊ አካባቢ የሚያደርስ አደገኛ ቦምብ መሆኑ ይነገራል፡፡


ዩክሬይን እና ሩሲያ ፈራሚዎች ባይሆኑም ክላስተር ቦምብ ከ100 በላይ እንዳይውል የተከለከለ መሆኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡



የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page