የውጭ ሀገር ፓስፖርት ያላችሁ ሁሉ የሆቴል አገልግሎት የሚያገኙት በውጭ ምንዛሬ እንዲሆን የሚያዘው የቆየ መመሪያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን የሚያስታግስ በመሆኑ ቁጥጥሩ ሊበረታ ይገባል ተባለ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድም ካለፈው ሐምሌ 2 ጀምሮ የውጭ አገር ዜጎችን የትኬት አገልግሎት የሚያገኙት በውጭ ምንዛሬ ብቻ ይሆናል ብሏል፡፡
• ሆቴሎች የውጭ ፓስፖርት የያዘን ግለሰብ በብር ማስተናገድ የሚችሉት ይዞት የመጣውን የውጭ ምንዛሬ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በህጋዊ መንገድ ወደ ብር የመነዘረበትን ተመጣጣኝ ሰነድ ካገኙ ብቻ ይሆናል፡፡
• ኢትዮጵያውያን ወደ ውጭ ለሚያደርጉት በረራ እንደቀድሞው በብር ትኬት መቁረጥ ይችላሉ፡፡
• በኢትዮጵያ ያሉ የተለያዩ ሃገራት አየር መንገዶች ጨምሮ የውጭ ሃገር ዜጎችን (የዲፕሎማቲክ ፈቃድ ያላቸውን ጨምሮ) በውጭ ምንዛሬ ብቻ የትኬት አገልግሎት እንዲሰጡ ይገደዳሉ፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Comments