የፋይናንስ አካታችነትን ለማስጓዝ ወደ ሥራ የገባው ቴሌ ብር እስካሁን በኢኮኖሚ ውስጥ 679.2 ቢሊየን ብር መላወሱን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ኩባንያው በዘንድሮ በጀት ዓመት በገቢ ደረጃ የእቅዴን 101% አሳክቻለሁ ብሏል።
75.8 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ሰምተናል።
ከአለምአቀፍ ኢንተርኮኔክት ሮሚንግ፣ ከመሠረተ ልማት ኪራይና ከሐዋላ አገልግሎት 164.1 ሚሊየን ዶላር በበጀት ዓመቱ ተገኝቷል ብሏል።
4.23 ቢሊየን ብር ወይም 78.4 ሚሊየን ዶላር ለብድር ተከፍሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም በዘንድሮ በጀት ዓመት 20.8 ቢሊየን ብር ግብር መክፈሉን ተናግሯል።
የደንበኛ ቁጥር 72 ሚሊየን ደርሷል መባሉን ሰምተናል።
ይህ ውጤት በውድድር ገበያ ደንበኞችን ለማቆየት በተሠራው ሥራ የመጣ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።
ኩባንያው አገልግሎት ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎችን በተቻለው ፍጥነት ማስጀመሩን ዛሬ የዓመቱን አፈፃፀም በተናገረበት ግዜ ተናግራል።
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
https://bit.ly/33KMCqz
Yorumlar