ሐምሌ 12፣2015 - ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ተጨማሪ ክስ ሊመሰረትብኝ ይችላል አሉ
- sheger1021fm
- Jul 19, 2023
- 1 min read
ጉዳዩ ከ3 ዓመታት በፊት የአሜሪካ እንደራሴዎች መምከሪያ የሆነው ካፒቶል ሂል በትራምፕ ደጋፊ ነውጠኞች ከተወረረበት ድርጊት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ፖለቲኮ ፅፏል፡፡
ትራምፕ በዚህ ጉዳይ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ነግረውኛል በሚል በድረ ገፅ ላይ ፅሁፍ ማስፈራቸው ታውቋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ብሎ ከሀላፊነት ከተነሱ በኋላ በጣም በርካታ ጥብቅ መንግስታዊ ሚስጥራዊ ሰነዶችን በመኖሪያ ቤታቸው አከማችተዋል በተባለበት ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡
ትራምፕ አስቀድሞ የችሎት ጉዳያቸው ከአሜሪካ ምርጫ በኋላ እንዲሆንላቸው ጥያቄ እያነሱ ነው፡፡
የቀድሞው ፕሬዘዳንት በመጪው አመት ምርጫ ሪፖብሊካዊውን የፖለቲካ ማህበር ወክለው በፕሬዘዳታዊ እጩነት ለመቅረብ ከተነሱ ቆይተዋል፡፡
የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…https://bit.ly/33KMCqz
Comments