ሐምሌ 13፣2015 - ሩሲያ በጥቁር ባህር ወደቦች የሚገኙ የዩክሬይንን የእህል ማከማቻ መጋዘኖች በሚሳየሎች እየመታች ነው ተባለ
- sheger1021fm
- Jul 20, 2023
- 1 min read
በጥቂቱ 60,000 ቶን እህል ማውደሟን ቢቢሲ የዩክሬይንን ሹሞች ዋቢ አድርጎ ፅፏል፡፡
ሩሲያ ሰሞኑን በዩክሬይን የእህል ምርት መለኪያ መሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየፈፀመች ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት የዩክሬይን የጥቁር ባህር ወደቦች ለመርከቦች መስተንግዶ አደገኛ እየሆኑ መምጣታቸው ተጠቅሷል፡፡
ዩክሬይን የእህል ምርቷን በጥቁር ባህር ወደቦች በኩል እንድትልክ የሚጠይቀው ስምምነት ያበቃው ሰሞኑን ነው፡፡
ስምምነቱ ያበቃለት ሩሲያ ከእንግዲህ አያሻኝም በማለቷ እንደሆነ ታውቋል፡፡
የሩሲያም ምርት ለአለም ገበያ እንዲቀርብ የሚጠይቅ የነበረ ቢሆንም በምዕራባዊያን ማዕቀብ እና መሰናክል ይሄ የስምምነቱ ክፍል ተግባራዊ አለመደረጉ ሞስኮ ከስምምነቱ እንድትወጣ አስገድዷታል ይባላል፡፡
በዚህ ረገድ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምዕራባዊያንን በአሻጥር ፈፃሚነት መክሰሳቸው ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…https://bit.ly/33KMCqz
Comments