top of page

ሐምሌ 15፣ 2016 - ወጋገን ባንክ ከቀና ሶፍትዌር ዲዛይን ጋር በመተባበር “እፎይታ” የተሰኘ የዲጂታል ብድር አገልግሎት ጀመረ

“እፎይታ” የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የዲጂታል ብድር አገልግሎት መሆኑን ባንኩ ለሸገር በላከው መግለጫ ተናግሯል።

 

እፎይታ የዲጂታል ብድር አገልግሎት  በዋናነት በጥቃቅን አነስተኛ እና መካከለኛ የንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ነጋዴዎች የንግድ ማስፋፊያ እና የስራ ማስኬጃ ካፒታል ለማሟላት እንዲሁም ለደሞዝተኞች የአስቸኳይ ጊዜ ብድር እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን  የወጋገን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን   አስረድተዋል ፡፡

 

የዲጂታል ብድር አገልግሎት መጀመር የስራ ፈጠራ ሀሳብ እያላቸው በገንዘብ እጥረት ምክንያት ያለሙትን ማሳካት ላልቻሉ በርካታ ሰዎች እቅዳቸውን ማስፈፀም የሚያስችላቸውን የፋይናንስ አቅርቦት ማመቻቸት የሚያስችል መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

 

የክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ቺፍ ኢምፓክት ኦፊሰር የሆኑት ወ/ሮ ሀያት አብዱልማሊክ በኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 3.2 ሚሊዮን የሚጠጉ አስተኛ እንዲሁም 7.8 ሚሊዮን ጥቃቅን የንግድ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ዜጎችን የስራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት እንደሚያጋጥማቸው አስረድተዋል።

 



በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ እና መረጃ መሰረት አድርጎ የለማው እፎይታ የዲጂታል ብድር አገልግሎት የፋይናንስ አቅርቦትን ችግር የሚፈታ እንደሆነ ተማምነውበታል፡፡

 

የእፎይታ የዲጂታል ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን በቅድሚያ ደንበኞች በወጋገን ባንክ ሂሳብ መክፈት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

 

በመቀጠልም የእፎይታ ብድር አገልግሎት የሞባይል መተግበሪያን ከፕሌይስቶር በማውረድ የብድር ጥያቄያቸውን በማቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

 

ወጋገን ባንክ በአሁኑ ወቅት በመላው ሀገሪቱ  438 ቅርንጫፎች፣ በ388 የኤቲኤም እና 436 የክፍያ መፈፀሚያ (ፓስ) ማሽኖች ፣ በ4,700 ወኪሎች እንዲሁም የኢንተርኔት እና ሞባይል ባንኪንግ የዲጂታል አገልግሎት አሉኝ ብሏል፡፡


 

 

Comments


bottom of page