top of page

ሐምሌ 17፣2015 - የዩክሬይንና የሩሲያ፤ የእህልና የማዳበሪያ ምርት በአፋጣኝ ለአለም ገበያ እንዲቀርብ ተጠየቀ

  • sheger1021fm
  • Jul 24, 2023
  • 1 min read

ቻይና የዩክሬይንም የሩሲያም የእህልና የማዳበሪያ ምርት በአፋጣኝ ለአለም ገበያ የሚቀርብበት መላ እንዲመታ ጠየቀች፡፡


የቀዳሚው ስምምነት የጊዜ ገደብ ባለፈው ሳምንት አብቅቷል፡፡


ስምምነቱ የዩክሬይን የእህል እና የማዳበሪያ ምርት በጥቁር ባህር ወደቦች በኩል ለአለም ገበያ እንዲቀርብ የሚጠይቅ ነበር፡፡


ለሩሲያም ተመሳሳይ እድል ቢያስቀምጥም በምዕራባዊያን ማዕቀብ እና እንቅፋትነት የስምምነቱ ክፍል ስራ ላይ ሳይውል ቆይቷል፡፡


በዚህም የተነሳ ሩሲያ የስምምነቱን መቀጠል አልሻም ማለቷን አናዶሉ አስታውሷል፡፡


አሁን ግን ለመፍትሄው የዩክሬይንም የሩሲያም ምርት ለአለም ገበያ የሚቀርብበት መላ እንዲመታ መጠየቋ ተሰምቷል፡፡



የኔነህ ከበደ


ሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page