top of page

ሐምሌ 18፣ 2016 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሻሽሎ ያቀረበውን ሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ዛሬ ያስተዋወቀው ሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ አንድ ጊዜ ብቻ ከመደበኛ ሂሳብ ጋር በማስተሳሰር በቀላሉ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚያስገኝ መሆኑ ተነግሮለታል ።


የባንኩ ቅርንጫፍ ጋር መሄድ ወይንም ኤጀንት ወይም ደግሞ ሌላ መተግበሪያ መጠቀም ሳያስፈልግ፤ ከመደበኛ የባንክ ሂሳብ ወደ ሲቢኢ ብር ፕላስ ገንዘብ ማስገባት እንደሚቻል ተነግሯል።


ነዳጅ ለመቅዳት በሲቢኢ ብር ፕላስ ላይ በቂ ገንዘብ ባይኖርም በዚያው ከመደበኛ ሂሳብ ላይ ተቀናሽ ሆኖ መክፈል እንደሚያስችልም ተጠቅሷል።


ከመደበኛው የሂሳብ ቁጥር ወደ ሌላ ሂሳብ ቁጥር ተሻሽሎ በቀረበው ሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ አማካኝነት በቀጥታ ገንዘብ መላክ ይቻላል ሲባል ሰምተናል።


ሲቢኢ ብር ፕላስ ሌላው ልዩ የሚያደርገው በአንድ ጊዜ እስከ አምስት ሰው ድረስ ገንዘብ መላክ ማስቻሉ ነው ተብሏል።

የባንኩ የሰው ሃይል ም/ፕሬዚደንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተፈፀመ ከ1.56 ቢሊዮን ብር የሚበልጥ የገንዘብ ዝውውር ወይም 31.6 ትሪሊዮን ብር ውስጥ በዲጂታል ባንኪንግ አማራጮቻችን የተፈፀመው 72 ከመቶ ድርሻ ይዟል ብለዋል።


የሲቢኢ ብር አገልግሎት የሚጠቀሙትን ደንበኞች ብዛትም 12 ሚሊዮን መድረሳቸውም ተነግሯል። 


ጥሬ ገንዘብ አልባ ግብይትን ለሁሉም ማህበረሰብ ክፍል ለማዳረስ የሲቢኢ ብር አገልግሎት እጅግ ጉልህ ሚና እንዳለው ባንካችን ያምናል ያሉት አቶ ኤፍሬም በዚህም ባለፉት አመታት በአገልግሎቱ ላይ የነበሩትን ችግሮችና የተጠቃሚዎችን ቁጥር ማነስ ለማስተካከል የአገልግሎት ማሻሻያ አድርገናል ብለዋል፡፡


ይህ የአገልግሎት ማሻሻያ ከዩኤስኤስ ዲ በተጨማሪ፤ በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት የሲቢኢ ብር አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን ከዚህ በፊት ይሰጡ የነበሩ የክፍያና ገንዘብ ዝውውር አማራጮችን አስፍቶ የተዘጋጀ  ነው ሲባል ሰምተናል፡፡


የባንኩ ደንበኞች ሲቢኢ ብር ፕላስን እንዲጠቀሙበት አቶ ኤፍሬም ጥሪ አቅርበዋል፡፡  


ንጋቱ ሙሉ

Comments


bottom of page