በተለያየ ምክንያት ፈቃዳቸው የተሰረዙ የ1700 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ሃብትና ንብረት አጣርቶ ተመሳሳይ አላማ ላላቸው ሌሎች ድርጅቶች ለማስተላለፍ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተናገረ።
#የሲቪል_ማህበረሰብ_ድርጅቶች ባለስልጣን ህልውናቸውን ያላረጋገጡና የተሻሻለውን አዋጅ ተከትሎ ዳግም ምዝገባ ያላደረጉ ድርጅቶችን ፍቃድ መሰረዙን ተናግሯል።
ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ህልውናቸውን አላረጋገጡም በሚል የሰረዛቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፤ የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን እና የስራ ክንውናቸውን የተመለከተ ሪፖርት ያላቀረቡ ናቸው ተብሏል።
እነዚህ ቁጥራቸው 205 እንደሆነ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ነግረውናል።
1500 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ደግሞ በአዲሱ አዋጅ መሰረት ዳግም ምዝገባ ባለማካሄዳቸው የተሰረዙ ናቸው ብለዋል አቶ ፋሲካው።
በሁለቱም ምክንያቶች የተሰረዙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሃብትና ንብረት ተጣርቶ፤ ተመሳሳይ አላማ ላላቸው ሌሎች ድርጅቶች እንዲተላለፍ ይደረጋል፤ ካልሆነም ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ፈንድ ገቢ ይሆናል ተብሏል።
ድርጅቶቹ ተደጋጋሚ ጥሪ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ተደርጎላቸው ካልቀረቡ እንዴት ተገኝተው ሃብት ንብረታቸው በምን መንገድ ለሌሎች እንዲተላለፍ ሊደረግ ይችላል?
ንጋቱ ረጋሳ
Commentaires