top of page

ሐምሌ 19፣ 2016 - የመልካ ቁንጥሬ ባልጪት የአረኪዮሎጂ ስፍራ በትምህርት ባህልና ሳይንስ ድርጅት(ዩኔስኮ) ተመዘገበ

የመልካ ቁንጥሬ ባልጪት የአረኪዮሎጂ ስፍራ በትምህርት ባህልና ሳይንስ ድርጅት ዩኔስኮ ተመዘገበ፡፡


በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዓመታዊ ጉባዔ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአረኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሶስት መስፈርቶችን በማሟላት የዓለም ቅርስ ሆነ ተመዝግቧል፡፡


ስፍራው እንዲመዘገብ ያደረገው ከ2.5 ሚሊየን ዓመት እስከ መጨረሻው የድንጋይ ዘመን የሰው ልጅ ይጠቀምባቸው የነበሩ የድንጋይ መገልገያዎች የያዘ ስፍራ ነው፡፡

2.5 ሚሊየን ዓመት እድሜ ያላቸው የተለያዩ የሰውና የእንስሳት ቅሪተ አካሎች በብዛት የሚገኙበት በመሆኑ፣ የሰው ልጅ ከድንጋይ የተለያዩ መገልገያዎችን ወይም መሳሪያዎችን ይሰራ እንደ ነበር የሚያሳዩ ስምንት የባልጩትና ሌሎች የድንጋይ መሳሪያ ማምረቻ ሥፍራዎችን ይዞ የሚገኝ በመሆኑ ለምዝገባ አብቅቶታል ተብሏል፡፡

የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ይህ ቅርስ የተመዘገበው ሉሲ የተገኘችበትን 50ኛ ዓመት በሚከበርበት ሰዓት ነው፣ ቅርሱ ተጠብቆ እንዲቆይም የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡


መልካ ቁንጡሬ ባልጪት ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጂራ በሚወስደው መንገድ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዋሽ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ቋሚ የሚዳሰሱ ቅርሶች 12ኛው ነው፡፡


በረከት አካሉ


コメント


bottom of page