top of page

ሐምሌ 19፣ 2016 - የአስተዳደር በደል አድርሰዋል የሚል አቤቱታ በህዝቡ ቀርቦባቸው ለማስተካከል ፈቃደኛ ባልሆኑ 46 የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ተመሰረተ

የአስተዳደር በደል አድርሰዋል የሚል አቤቱታ በህዝቡ ቀርቦባቸው ለማስተካከል ፈቃደኛ ባልሆኑ 46 የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ተመሰረተ፡፡


የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን መርምሮ እልባት እንዲያገኙና አቤት ባዮችም እምባቸው እንዲታበስ እያደረግኩ ነው የሚለው የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም፤ የደረሱኝን አቤቱታዎች መርምሬ መፍትሄ እንዲያገኙ ከሰጠሁዋቸው በርካታ የመንግስት ተቋማት 46ቱ ያጠፉትን አስተካክሉ የሚል ምክረ ሃሳብ ብሰጥም ዳተኛ ሆነው በመገኘታቸው ለመክሰስ ተገድጃለሁ፡፡


ወደ ፍርድ ቤት ከሄዱት 46 ጉዳዮች 12ቱ ውሳሄ እንዳገኙ፤2ቱ በቅርቡ ውሳኔ ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና ቀሪዎቹ በሂደት ላይ እንዳሉ የነገሩን በኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ተወካይ እምባ ጠባቂ የሆኑት አቶ ደነቀ ሻንቆ፤ የተቋማቱን ማንነት ግን ከመናገር ተቆጥበዋል፤ምንነታቸውን ሁሉም ጉዳዮች በፍርድ ቤት ውሳኔ ካገኙ በኋላ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡



Comentarios


bottom of page