top of page

ሐምሌ 20፣ 2016 - ''ኢትዮጵያ ካላት አቅም አኳያ ሲታይ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እየቀነሰ መጥቷል''

በየዓመቱ መንግስት የሚሰበስበው የግብር መጠን እየጨመረ መጥቷል፡፡


በተጠናቀቀው 2016በጀት ዓመት 466 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር መናገሩ ይታወሳል፡፡


በየዓመቱም የገቢ አሰባሰቡ እየጨመረ መምጣቱን አሃዛዊ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡


ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ካላት አቅም አኳያ ሲታይ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እየቀነሰ መምጣቱን ጥናት አሳይቷል፡፡


ከሀገሪቱ ጥቅል ሀገራዊ ምርት ከፍተኛ ግብር የተሰበሰበው ከስምንት ዓመታት በፊት ሲሆን እሱም 14 በመቶ ነበር ፣ አሁን ግን ያለው ምጣኔ ከ10 በመቶ በታች መሆኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡



ያሬድ እንዳሻው


Comentarios


bottom of page