top of page

ሐምሌ 24፣2016 - ብሔራዊ ባንክ፤ ወርቅ ለሚያቀርቡ አምራቾች እና አቅራቢዎች ክፍያ የሚፈጸመው፤ በየዕለቱ በማወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን ተሰልቶ ነው አለ

  • sheger1021fm
  • Jul 31, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ወርቅ ለሚያቀርቡ አምራቾች እና አቅራቢዎች ክፍያ የሚፈጸመው፤ በየዕለቱ በማወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን ተሰልቶ ነው አለ፡፡


ባንኩ በወርቅ መግዣ ላይ አዲሱን አሰራር ተግባራዊ ያደረገው፤ የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ የሚመራ መደረጉን ተከትሎ ነው።


እ.ኤ.አ ከ ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለማንኛዉም ወርቅ አቅራቢ ክፍያ የሚፈጸመዉ፤ የእለቱን ዓለም ዓቀፍ የወርቅ ዋጋ በእለቱ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣዉ የዉጭ ምንዛሪ ተመን ተባዝቶ ይሆናል ብሏል ማዕከላዊ ባንኩ፡፡


#ወርቅ አምራቾችና አቅራቢዎች የእለቱን የዉጭ ምንዛሪ ተመን ከብሔራዊ ባንክ ድረ-ገጽ ላይ እንደሚያገኙ ባንኩ ተናግሯል፡፡


ለሚያቀርቡት ወርቅ ክፍያዉን ወርቁን ከሸጡበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በእለቱ ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page