top of page

ሐምሌ 24፣2016 - ኢትዮጵያ ከዓም አቀፍ የልማት አጋሮች ካገኘቸው 1.5 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር ሲሆን ይህም በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ ከዓም አቀፍ የልማት አጋሮች ካገኘቸው 1.5 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ብድር ሲሆን ይህም በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው ተባለ፡፡


በብድር መልክ የተገኘው ከወለድ ነጻ እና የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜም አለው ተብሏል፡፡


የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ በደረገው ስብሰባ ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት (የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር) አጸድቋል፡፡


ከዓለም ዐቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት የ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በእርዳታ፣ 500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ተናግሯል፡፡


የፋይናንስ ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች ለማስፈጸም በተለይም ለሥራ ፈጠራ፣ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለመቅረፍ፣ የመዋቅር ማስተካከያ ለማድረግ እንዲሁም የፌደራል መንግሥት የ2ዐ17 ዓ.ም በጀትን በቀጥታ ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል፡፡


የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰነዱ ላይ ከተወያየ በኋላ ብድሩ ከወለድ ነፃ ፣ የ6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ እንዲሁም ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋገጥ ስምምነቱን አጽድቆ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል ተብሏል፡፡

Σχόλια


bottom of page