top of page

ሐምሌ 24፣2016 - ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ በገበያው አማካይነት እንዲወሰን የሚያደርግን ያካተተ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ስራ ላይ አውላለች

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በሚቀጥሉት 4 ዓመታት 8 በመቶ ያህል እንዲያድግ ያደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡


የዋጋ ንረቱ አሁን ካለበት 19 በመቶ ወደ 10 በመቶ፣ የታክስ ገቢ ከአጠቅላይ ሀገራዊ ምርቱ ያለው ምጣኔ አሁን ካለበት 7 በመቶ ወደ 35 በመቶ በአራት አመታት ውስጥ ያሳድገዋል የሚል እቅድ ይዟል፡፡


የወጪ እና ገቢ ንግድ ዋጋም ወደ 20 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል፣ ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትም ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር ያድጋል የሚል ግምት ተወስዷል፡፡


#የውጭ_ምንዛሪ በገበያው አማካይነት እንዲወሰን መደረጉን በበጎ ጎኑ የሚመለከቱት የኢንቨስትመንት አማካሪው አቶ ከፈለኝ ሃይሉ ውሳኔው የሚፈለገውን እንዲያመጣ በርካታ ስራዎች ይጠበቃሉ ይላሉ፡፡


ከዚህ ቀደም መሰራት የነበረባቸው ፣አሁንም ያልተፋቱ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ላይ ያሉ ችግሮችን እዚህ ጋር ባለሞያው ይጠቅሳሉ፡፡


ምርት አምርቶ ከሀገርም ተርፎ የውጭ ምንዘሪ ሊያስገኙ የሚችሉ ስራዎችን ተብትበው የያዟቸው በርካታ ችግሮች መኖራቸውን የሚያነሱት አቶ ከፈለኝ ከዚህም መካከል የፀጥታ ስጋት እና በዓለም ላይ 159ኛ ላይ ሀገሪቱ ያለችበትን ስራን ለመስራት አስቻይ ሁኔታ (ease of doing business) ይጠቅሳሉ፡፡


#ብሔራዊ ባንክ ማክሮ ፋይናንስ ላይ አንደወሰደው እርምጃ ሁሉ በሀገር ውስጥ ምርት በብዛት አንዲመረት የሚያስችሉ ማበረታቻዎችን፣ማነቆዎችን የሚፈቱ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ማውጣት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡


በዚህ ዘርፍ ደግሞ ቀዳሚው ስራ ምርትን በጥራትም በብዛትም ለአለም ገበያ ማቅረብ ነው አሁንም ግን ለውጭ ገበያ የምናቀርበው ጥሬ ቡና፣ የቅባት እህሎች ቆዳ እና ሌጦ መሆኑ ከፍተኛ ስራ ይጠይቃል ሲሉ ባለሞያው ያስረዳሉ ፡፡


ኢትዮጵያ በዓመት ምርቶቿን ወደ ውጭ ልካ የምታገኘው ዶላር ለነዳጅ መግዣ እንኳን አይበቃም፡፡

ወጪ ንግዱ 4 ቢሊዮን ዶላር መሙላት አልቻለም፡፡


በአንፃሩ ሀገሪቱ 14 ቢሊዮን የሚያወጡ ምርቶችን ከውጭ ትገዛለች፡፡


የንግድ ሚዛን ጉድለቱን ለመሙላት ወጪ ንግዱ መበርታት አለበት፡፡


የንግድ ሚዛን ጉድለቱን ለማጥበብ ምርት ላይ ካልተሰራ፣ የመጪ ንግድ ምርቶች በአይነትም በብዘታም ማምረት ካልተቻለ ክፍተቱ እየሰፋ መሄዱ አንደማይቀር አቶ ከፈለኝ ስጋታቸወን ነግረውናል፡፡


ምርት በሀገር ውስጥ አንዳይመርት በረካታ #ችግሮች መኖራቸወን የሚጠቅሱት አማካሪው አንዱ አና ዋነኛው ችግር የነበረው የውጪ ምዛሬ እጥረት ነበር አሱ በአዲሱ ፖሊስ የሚፈታ ይመስላኛል ይህንን እድል ተጠቅሞ ምርት ማሳደግ ላይ ግን ብዙ አንቅፋቶች አሉ ብለዋል፡፡


ዜጎች በሀገሪቱ ውስጥ ተረጋግተው የሚችሉበት ሁኔታ አለመኖር፣ የመስሪያ ቦታ እጦት፣ የሃይል አቅርቦት፣ የብድር አቅርቦት አን ሌሎች ችግሮች አሉ በዚህ ሁኔታ ደግሞ ወጪ ንግዱን ማሰደግ አይቻልም ብለዋል፡፡


በሀገር ውስጥ መመረት የሚችሉ ግን ደግሞ ከውጭ በዶላር ተገዝተው የሚገቡ ምርቶች በሀገር ውስት የመተካት ጉዳይ ለማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ ማሳካት የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን አማካሪው ነግረውናል፡፡


ሰው በሀገር ሰርቶ እርሱም ተጠቅሞ ሀገርም እንድትጠቅም የንብረት መብትን እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የኢንቨስትመንት አማካሪ ከፋለኝ ሃይሉ ተጠቅሰዋል፡፡


ንጋቱ ሙሉ



Comments


bottom of page