ኢትዮጵያ በየዓመቱ በሚሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ የአፈር ማዳበሪያ ከውጪ ሀገር ታስገባለች፡፡
ገበሬው ማዳበሪያውን ለማግኘት በአስር ሺህዎች ብር ወጪ በማድረግ ለማሳው ገዝቶ ይጠቀማል፡፡
አሁን ይህንን ችግር የሚቀርፍና 2,000 በማይሞላ ብር ‘’ኦርጋኒክ ማዳበሪያ’’ መስራት የጀመረ የፈጠራ ባለሞያ መጥቷል፡፡
የስራው የፈጠራ ስራው የሰራው ባለሙያ ለስራው ከመንግስት በቂ ድጋፍ እየተደረገልኝ አይደለም እያለ ሲሆን ምርቱን ለመጠቀም ከኢትዮጵያ ይልቅ ሌሎች የተሻለ ፍላጎት እያሳዩ ነው ሲል ተናግሯል፡፡
በተለይም ኬንያ እና ሩዋንዳ የተሻለ ፍላጎትና ድጋፍ እያደረጉልኝ ነው ብሏል የፈጠራ ስራውን የሰራው አቶ ሳምሶን አለሙ፡፡
ማዳበሪያው ከተለያዩ ገበሬዎች ጋር ማሳላይ ተሞክሮ ከፋብሪካው ማዳበሪያ የተሻለ መሆኑን ታይቷል ያለ ሲሆን በተለይም #በአሲድ የተጠቃ አፈርን ለማከምና መሬቱ የተሻለ ምርት እንዲሰጥ ያደርጋል ብሏል፡፡
ይህ #የአፈር_ማዳበሪያ የተዘራው ዘር እስከ 90 ከመቶ ምርት እንዲሰጥ ያደርጋል የሚለው የፈጠራ ባለሙያው ማዳበሪያው እዚሁ ሀገር ቤት የሚዘጋጅ ነው ሲል ያስረዳል፡፡
ኦርጋኒክ ማዳበሪያው እዚሁ ሀገር ቤት የሚመረት በመሆኑ ሀገሪቱ ለዚህ የምታወጣው የውጪ ምንዛሪ ከመቀነሱም ባለፈ ለአንድ ሄክታር የሚያስፈልገው ኦርጋኒክ ማዳበሪያ 2 ኪሎ እንኳን የማይሞላ መሆኑን አቶ ሳምሶን ተናግሯል፡፡ ምርታማነቱም በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ያደርጋል ነው የሚለው፡፡
ዋጋው ምን ያህል ነው? የህብረተሰቡን አቅም ያማከለ ይሆን ስንል አቶ ሳምሶን የጠየቅናቸው ሲሆን 1 ነጥብ 5 ኪሎ የሚሆነው ኦርጋኒክ ማዳበሪያ ከ1ሺህ ብር እስከ 1 ሺህ 500 ብር በአሁን ሰዓት ለገበሬው ይቀርባል፡፡
ምርቱ በይበልጥ ለማምረት ፍላጎት ቢኖርም መንግስት የሚሰጠው ድጋፍ በጣም አነስተኛ ነው የተባለ ሲሆን እንደ ኬኒያ እና ሩዋንዳ ያሉ ሀገራት ግን በመንግስት ደረጃ ምርቱን ለማግኘት ፍላጎች አሳይተዋል፡፡
አሁንም ቢሆን መንግስት አስፈላጊው ድጋፍ ሊያደርግልን ይገባል የሚለው አቶ ሳምሶን ይህ ከሆነ ጥሩ ስራ መስራት እችላለሁ ይላል፡፡
በዚህ ሰዓት 8,000 የሚሆኑ ገበሬዎች ይህንን ኦርጋኒክ ማዳበሪያ እየተጠቀሙ ነው፡፡
በዚህ አመት ይህንን ቁጥር እስከ 200 ሺ ድረስ ለማድረስ ታቅዷል የተባለ ሲሆን በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ቢያንስ 5 ሚሊዮን አነስተኛ ማሳ ያላቸው ገበሬዎች ይህ ማዳበሪያ ተጠቃሚ ለማድረግ ውጥን ተይዟል፡፡
ማዳበሪያውን ለመጠቀምና ሀሳቡን ለማወቅ ከምሁራኑና ከመንግስት ኃላፊዎች ይልቅ ገበሬው በበለጠ እንደተረዳቸው የፈጠራ ባለሙያው ነግሮናል፡፡
በረከት አካሉ
ความคิดเห็น