ወታደራዊ የመንግስት ግልበጣ በተደረገባት ኒጀር ኤሌክትሪክ እየጠፋ እና እየተቋረጠ መሆኑ ተሰማ፡፡
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ለAFP እንደተናገሩት ችግሩ ያጋጠመው የናይጄሪያው የኤሌክትሪክ ኩባንያ አቅርቦቱን በማቋረጡ ነው፡፡
እንደሚባለው የናይጀሪያው ኩባንያ ወደ ኒጀር የሚያልፈውን ኤሌክትሪክ ከትናንት በስቲያ አንስቶ አቋርጦታል፡፡
ባለፈው እሁድ በናይጀርያዋ መዲና አቡጃ የተሰበሰቡት የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት ምጣኔ ሐብታዊ ማህበር /ኢኮዋስ/ መሪዎች በኒጀር ላይ ማዕቀብ እንደጣሉ ዘገባው አስታውሷል፡፡
የኤሌክትሪክ መጥፋቱም የማዕቀቡ አካል ሳይሆን አይቀርም ተብሏል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments