ሐምሌ 27፣2015 - አትሚስ በሶማሊያ የወታደሮች ቅናሽ ማድረጌን እቀጥላለሁ አለ
- sheger1021fm
- Aug 3, 2023
- 1 min read
በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰራዊት /አትሚስ/ በዚያ የወታደሮች ቅናሽ ማድረጌን እቀጥላለሁ አለ፡፡
ለሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰራዊት ተልዕኮ ሰራዊት ያዋጡ አገሮች የጦር ሹሞች በቅርቡ በርዕሰ ከተማዋ ሞቃዲሾ በጉዳዩ ላይ እንደተነጋገሩ ዘ ኢስት አፍሪካን ፅፏል፡፡
አዛዦቹ በመጪው መስከረም ወር ተጨማሪ 3 ሺህ ወታደሮችን እንደሚያስወጡ ተናግረዋል፡፡
አትሚስ ከሰራዊት ቅናሽ በተጨማሪ ደረጃ በደረጃ የጦር ሰፈሮችንም በማስረከብ ላይ ይገኛል፡፡
እስካሁንም 6 የጦር ሰፈሮችን ማስረከቡን ዘገባው አስታውሷል፡፡
አትሚስ ደረጃ በደረጃ ወታደሮቹን እየቀነሰ ቢሆንም በአገሪቱ የአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ስጋትነት ገና እንዳልቀነስ ይነገራል፡፡
የኔነህ ከበደ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments