የኒጀር ወታደራዊ የመንግስት ገልባጮች ሀገሪቱ ከአሜሪካ፣ ከፈረንሳይ፣ ከናይጀርያ እና ከቶጎ ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጡት፡፡
የኒጀሮቹ ገልባጮች ህጋዊውን የፕሬዘዳንት ሞሐመድ ባዙምን መንግስት ወደ ሀላፊነቱ እንዲመልሱ ግፊት እንደበረታባቸው አናዶሉ ፅፏል፡፡
በዚሁ ጉዳይ የኒጀሮቹን የመንግስት ገልባጮች ለማነጋገር ወደ ሀገሪቱ አምርቶ የነበረው የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት ምጣኔ ሐብታዊ ማህበር /ኢኮዋስ/ የልዑካን ቡድን ያለ አንዳች ውጤት መመለሱ ታውቋል፡፡
ኤኮዋስ ገልባጮቹ የባዙምን መንግስት ወደ ሀላፊነቱ እንዲመልሱ የሰጣቸው የ7 ቀናት የማስጠንቀቂያ ገደብ ነገ ያበቃል፡፡
የናይጀሪያው ፕሬዘዳንት ቦላ ቱኑቡ የሀገሪቱ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት /ሴኔት/ የናይጀሪያ ጦር ወደ ኒጀር እንዲዘምት ይሁንታውን እንዲያረጋግጥ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡
የኔነህ ከበደ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments