top of page

ሐምሌ 29፣2016 - በወላይታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

  • sheger1021fm
  • Aug 5, 2024
  • 1 min read


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ፤ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል፡፡


በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሕዝቅኤል ጎቶሮ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ተናግረዋል፡፡


#በሌላ_በኩል በቀሪ የክረምት ወራቶች ተደጋጋሚ የሆነ የመሬት መንሸራተት ሊኖር እንደሚችል የኢትዮጵያ ሜቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ አስጠንቅቋል፡፡


የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ በቀሪ የክረምቱ ቀናት ክረምቱ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ስለሚኖር፤ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች እንዲከወኑ አሳስበዋል፡፡


በመጪው ነሐሴና መስከረም ወራቶች ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ስለሚኖር የመሬት መንሸራተት፣ የውሃ መተኛት፣ ጎርፍ፣ የወንዝና የግድቦች ሙላት፣ የሰብል በሽታ፣ የአፈር መሸርሸር እንደሚኖር ተነግሯል፡፡


በደሴ ከተማ፣ አባይ ተፋሰስ አካባቢ፣ በወላይታ ኮይሻ አካባቢና ሌሎችም ቦታዎች ላይ የመሬት መንሸራተት ሊከሰረት እንደሚችል ትንበያው አመላክቷል።



ትዕግስት ዘሪሁን / ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page