ሐምሌ 30፣2016 - ተፈናቃዮች የተጠለሉበት የመጠለያ ጣቢያዎች ዝናብና ነፋሱን መቋቋም ስላልቻሉ ተፈናቃዮቹ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው
- sheger1021fm
- Aug 6, 2024
- 1 min read
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የተጠለሉበት የመጠለያ ጣቢያዎች ዝናብና ነፋሱን መቋቋም ስላልቻሉ ተፈናቃዮቹ ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው፡፡
መጠለያም የሚሰጠንም ሆነ ያሉትን የሚጠግንልን አጥተናል ብለዋል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት በበኩሉ ስለችግሩ ለክልሉም ሆነ ለፌደራል መንግስት አሳውቄ መልስ ማግኘት አልቻልኩም ብሏል፡፡
በጃራ መጠለያ ጣቢያ 11,386 ተፈናቃዮች ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን የመጠለያ ጣቢያ ችግር እንደገጠማቸው ተናግሮዋል፡፡
ችግሩ ጃራ የመጠለያ ጣቢያ ብቻ ሳይሆን ወልድያ እና ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንደገጠማቸው የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ይመር ተናግረዋል፡፡
Comentários