top of page

ሐምሌ 30፣2016 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ግብይታቸው በዶላር ለሚደረጉ የዓለም-አቀፍ በረራዎች ላይ የደረኩት የተለየ ለውጥ የለም ሲል ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Aug 6, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ግብይታቸው በዶላር ለሚደረጉ የዓለም-አቀፍ በረራዎች ላይ የደረኩት የተለየ ለውጥ የለም ሲል ተናገረ፡፡


የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የአውሮኘላን ቲኬት ዋጋን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡


አየር መንገዱ የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ ላይ የተደረገውን የውጭ ምንዛሪ ማስተካከያ ተከትሎ የዓለም-አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ጉዞ #የአውሮኘላን_ቲኬት_ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል የሚል መረጃ በተለያዩ የበይነ-መረብ የመገናኛ ብዙሃን መሰራጨቱን አስውያለሁ ብሏል።


በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት አሠራር የዓለም-አቀፍ ጉዞ የአውሮኘላን ቲኬት ዋጋ የሚተመነው በአሜሪካን ዶላር ወይም በተመሳሳይ ገንዘቦች (Currency) ነው፤ ይሁን እንጂ መንገደኞች በየሀገሩ ቲኬት ሲገዙ በሀገሩ ገንዘብ ተመንዝሮ ሊከፍሉ ይችላሉ ብሏል።


የቲኬቱ ዋጋ የሚወሰነው ቲኬቱን በሚገዙበት ቀን የሀገሩ ገንዘብ ባለው #የዶላር የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ተሰልቶ ነው፤ ይህም ሁሉም አየር መንገዶች የሚጠቀሙበት ዓለም- አቀፋዊ አሠራር ነው ሲል አስረድቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግብይታቸው በዶላር ለሚደረጉ የዓለም-አቀፍ በረራዎች ላይ ያደረገው የተለየ ለውጥ የለም፤ ይሁን እንጂ ዓለም-አቀፍ ቲኬቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በብር ሲገዙ ጭማሪ የሚያሳየው የዶላሩ ዋጋ አሁን ገበያ ላይ ባለው የብር የውጭ ምንዛሪ መጠን ስለሚቀየር ነው።


ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ቲኬት የሚሸጡ ሁሉም ዓለም-አቀፍ አየር መንገዶች የሚጠቀሙበት አሠራር መሆኑን አየር መንገዱ ተናግሯል፡፡


በሌላ በኩል በሀገራችን በቅርቡ የተደረገውን #የውጭ_ምንዛሪ_ማስተካከያ ተከትሎ ለሀገር ውስጥ በረራ በቲኬት የብር ዋጋ ላይ አስከአሁን የተደረገ ለውጥ የለም ብሏል።


ይሁን እንጂ ከአውሮኘላኖች የግዢ እና የኪራይ ዋጋ እንዲሁም ክፍያቸው በውጭ ምንዛሪ ከሆኑ የአውሮኘላኖች ጥገና እና የመለዋወጫ ዕቃዋች ግዢዎች ጋር ተያይዞ ወደፊት #የሀገር_ውስጥ_በረራ የቲኬት ዋጋ ላይ በጥናት በተደገፈ መልኩ መጠነኛ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁሟል፡፡



ማንያዘዋል ጌታሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page