የስራ ቦታ እጦት፣ ስራ መጀመሪያ ወረት አለማግኘት፣ ንግድ ፍቃድ ለማውጣት ያለው ቢውሮክራሲ እና ውጣ ውረድ ከችግሮቹ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
እነዚህን ችግሮች ተቋቁመው ለእነሱም ሆነ ለሌሎች እንጀራ የፈጠሩ ቁጥራቸው ጥቂትም ቢሆነ አሉ።
ኬብሮን ግዛቸው እና እስክንድ ብርሃኑ ከእነዚህ መከካል የሚመደቡ ናቸው።
ኬብሮን ግዛቸውና ጓደኞቿ የዶሮ ጫጩት ማስፈልፈያ ማሽን እንኩቤይተር ሰርተዋል፡፡
‘’ከዚህ በፊት የአንድ ቀን የዶሮ ጫጩት ለማግኘት እረጅም ቀናትን መጠበቅ ግዴታ ነበር’’ ያለችው ኬብሮን ለዚህም ምክንያቱ ከውጪ ሀገር የሚገባው ማሽን ዋጋ መወደድ እና በአቅራቢያ አለመገኘቱ ነው ብላለች፡፡
ሌላው የፈጠራ ስራ ሲያቀርብ የተመለከትነው እስክንድር ብርሃኑ የዶሮ መኖ በሀገር ውስጥ ማምረት የሚቻልበት ሁኔታ የሚያሳይ የፈጠራ ስራ ነው፡፡
ለዶሮ መኖ ማቀነባበሪያ የሚሆኑ ግብአቶች ኢትዮጵያ ከውጪ እንደምታስገባ ያስታወሰው እስክንድር አዲሱ የፈጠራ ስራው ይህንን ክፍተት በቀላሉ ሚሞላ ነው ብሏል፡፡
የፈጠራ ስራው ከሀዋሳ ዩንቨርስቲ ጋር በመሆን እየሰሩት መሆኑን የነገረን ሲሆን ‘’የእውቅና ፈቃዱ ሲጠናቀቅ ከገበሬዎች ጋር በጋራ በመሆን ለማምረት አቅደናል’’ ሲል ነግሮናል፡፡
የስራ እና ክህሎት ሚንስቴር በበኩሉ ከዚህ በፊት የፈጠራ ስራ የነበራቸው ወጣቶች የሚያቀርቡትን የድጋፍ ክፍተት የፋይናንስ አቅርቦት ችግሮች እንደነበሩ ይናገራል፡፡
በስራ እና ክህሎት የፈጠራ ስራ ሀሳብ ማበልፀጊያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አደሬ እንደሚሉት አሁን የፈጠራ ሀሳብ የሚስተናገድበት ኢኔቬቲቭ ፈንድ ተቋቁሟል፡፡
የስራ እና ክህሎት ሚንስቴር ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ወጣቶች ወደ ስራ የሚገቡበት መንገድ ለማመቻቸት በጋራ እየሰሩ መሆኑን የነገሩን ሲሆን የፋይናንስ ተቋማትና የክህሎት ድጋፍ የሚያደርጉ የትምህርት ተቋማት እንዳሉ ነግረውናል፡፡
በረከት አካሉ
Comentários