top of page

ሐምሌ 9፣ 2016 - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከመደራጀቱ በፊት በለያቸው አምስት መሰረታዊ ነጥቦችን ዙሪያ እየሰራ ነው ተባለ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከመደራጀቱ በፊት በለያቸው አምስት መሰረታዊ ነጥቦችን ዙሪያ እየሰራ ነው ተባለ፡፡


በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርናና የገጠር ልማት ክላተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለሸገር እንደተናገሩት የክልሉ ሀብት ሰው መሆኑን በማስቀደም ክልሉ ከመደራጀቱ በፊት ትኩረት ከሰጠባቸው ነጥብ ውስጥ አንዱ ነው፤ የአካባቢው የሰላም ሁኔታም ሌላኛው ነው ብለዋል፡፡


የግብርና ምርትን በማሳደግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከውጪ የሚገቡ የምግብ እህሎችንና ሰብሎችን በክልሉ ማምረትና መተካት ሌላው ጉዳይ መሆኑን ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ ነግረውናል፡፡


የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን በገጠር ማስፋፋትም ቀደም ሲል ክልሉ ከመደራጀቱ በፊት ከተለዩ ነጥቦች ማዕከል እንደሚገኙበትም ተሰምቷል፡፡



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page