top of page

መስከረም 11፣2017 - የፀረ HIV መድሃኒት ተጠቃሚዎች እና የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ተጠቂዎች የሚያገኙትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ ስምምነት ተደረገ

በኢትዮጵያ የፀረ ኤች አይቪ ኤድስ(HIV) መድሃኒት ተጠቃሚዎች እና የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ተጠቂዎች የሚያገኙትን አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ ስምምነት ተደረገ፡፡


ስምምነቱን ያደረጉት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይቪ ኤድስ እርዳታ ፔፕፋር እና ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ናቸው፡፡


በአሜሪካ የፕሬዝዳንቱ የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይቪ ኤድስ እርዳታ ፔፕፋር ባለፉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ኤች አይቪ ኤድስን ለመከላከልና ተጠቂዎችን ለመርዳት የሚሆን 3 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡


በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ፔፕፋር ኮሚቲኒ ሊድ ሞኒተር ፕሮግራም በሚል እየከወነው ያለው ስራ እራሱ ማህበረሰቡ ተሳታፊ ያደረገ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ቀጣይነት ያለው መሰረተ ልማት ለመገንባት ነው ብለዋል፡፡


የጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ይርጋለም ኮሚኒቲ ሊድ ሞኒተር ፕሮግራም የፀረ ኤች አይቪ ኤድስ መድሀኒት ተጠቃሚ ሰዎች በጤና ተቋማት የሚያጋጥማቸው ችግሮችን ለመፍታት ይረዳል ብለዋል፡፡


ይህ ሲሆን የማህበረሰቡ እና እራሳቸው አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ሰዎች ስለሚሳተፉ ውጤታማ እንዲሆን ያግዛል ሲሉ ነግረውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምፅ ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ…



በረከት አካሉ

Comments


bottom of page