top of page

መስከረም 12፣2016 - በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የታጠበ የድንጋይ ከሰል ማምረቻ ፋብሪካ ተገንበቶ ስራ መጀመሩ ተነገረ

Updated: Oct 3, 2023


በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነና በዓመት እስከ 2.1 ሚሊዮን ቶን የታጠበ የድንጋይ ከሰል ማምረት ይችላል የተባለለት ፋብሪካ ተገንበቶ ስራ መጀመሩ ተነገረ፡፡


ፋብሪካው የተገነባው ዮ ሆልዲንግ ንግድ እና ማኑፋክቸሪንግ በተባለ የሀገር ቤት ኩባንያ ሲሆን የድንጋይ ከሰል በማምረትና በማቀነባበር ሒደቱ ደግሞ ከሁለት የህንድ ኩባንያዎች ጋር በትብብር ይሰራል ተብሏል፡፡


በሀገር ቤት ለሚገኙ ለሲሚንቶ፣ ለብረት፣ ለወረቀት፣ ለሴራሚክና ለሌሎች መሰል ምርት ለሚያመርቱ ድርጅቶች የታጠበ የከሰል ድንጋይ ግብዓት እንደሚያቀርብ የፋብሪካው የስራ ኃላፊዎች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል፡፡


ኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካኝ ከስከ 1 ሚሊዮን ቶን ሚደርስ የታጠበ የድንጋይ ከሰል ከውጭ እንደምታስገባ ሲነገር ሰምተናል።


ለዚህም ከ227 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደምታወጣ በመድረኩ የተነገረ ሲሆን የዚህ ፋብሪካ መገንባት ለድንጋይ ከሰል የሚወጣውን የውጭ ምነዛሪን በመቀነስ በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋልም ተበሏል፡፡


የኢትዮጵያ ዓመታዊ የድንጋይ ከሰል ፍላጎት 2.2 ቢሊዮን ቶን ይደርሳል የተባለ ሲሆን ዛሬ ስራ መጀመሩ የተነገረለት ዮ ሆልዲንግ ፋብሪካ በሰዓት 150 እንዲሁም በአመት 1 ሚሊዮን ቶን የታጠበ የድንጋይ ከሰል እንደሚያመርት ተጠቅሷል፡፡


ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ ተገንብቷል የተባለውና ከሁለት ስማቸው ካለተጠቀሰ የህንድ ኩባንያዎች ጋር በትብብር እንደሚሰራ የተነገረው የከሰል ድንጋይ ማምረቻ ፋብሪካው፤ በሙሉ አቅሙ ማመረት ሲችል በዓመት እስከ 2.1 ሚሊዮን ቶን የታጠበ የድንጋይ ከሰል ለፋብሪካዎች በግብዓትነት እንደሚያቀርብም በፋብሪካው የስራ ሀላፊዎች ታምኖበታል፡፡


ከአዲስ አበባ በ400 ኪ.ሜ ርቀት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተገነባው ፋበሪካው ለ700 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል ተብሏል፡፡



ማንያዘዋል ጌታሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page