top of page

መስከረም 14፣2017 - በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ቦታዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ጠየቀ

በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ከሚታሰቡ ቦታዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንፅላ ፅ/ቤት ጠየቀ፡፡


በሊባኖስና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ስጋት እንዲሁም ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መጥቷል ያለው ቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ በተለይ በደቡባዊ ሊባኖስ እና በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል፡፡

ቆንፅላ ፅህፈት ቤቱ ጉዳዩ አሳሳቢ መሆኑ ተረድቶ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር እየሰራ እንዳለ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ አስረገድቷል፡፡


ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን መተግበር የከፋ ነገር በሚያጋጥምበት ወቅት ደግሞ በቆንፅላው የቀጥታ የስልክ መስመር ዜጎች እንዲደውሉ ፅህፈት ቤቱ ጠይቋል፡፡


ችግሩ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ ወደፊት የሚወሰዱ እርምጃዎችን በፌስ ቡክ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ የማሳውቅ ይሆናል ብሏል፡፡


ያሬድ እንዳሻው

Comments


bottom of page