መስከረም 14፣2017 - በኦሮሚያ ክልል አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘው መፅሐፍ የሚያስፈልገው 72 ሚሊዮን ገደማ ቢሆንም እስካሁን ታትሞ ለተማሪዎች የደረሰው 26 ሚሊዮን ብቻ ነው ተባለ
- sheger1021fm
- Sep 24, 2024
- 1 min read
በኦሮሚያ ክልል አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘው መፅሐፍ የሚያስፈልገው 72 ሚሊዮን ገደማ ቢሆንም እስካሁን ታትሞ ለተማሪዎች የደረሰው 26 ሚሊዮን ብቻ ነው ተባለ፡፡
በሁለት ዓመታት ውስጥ 26 ሚሊየን መፅሐፍት ብቻ መታተሙን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተናግሯል፡፡
በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ለተማሪዎቹ መፅሐፍትን አንድ ለአንድ ማዳረስ ያልተቻለው የሀገር ውስጥ አታሚ ድርጅቶች የወረቀት እጥረት ስላጋጠማቸው ነው ተብሏል፡፡
በተያዘው የትምህርት ዘመን እጥረቱ በተወሰነ መልኩ እንዲቀረፍ ባሳለፍነው ሀምሌ እና ነሐሴ ወራት ብቻ ለአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች 3 ሚሊዮን መፀሐፍት እንዲታተም ተደርጓል የተባለ ሲሆን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር 2 ሚሊዮን መፅሐፍት ተሰጥቷል ተብሏል፡፡
አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘው የቅድመ አንደኛ እና የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች መፅሀፍ የህትመት ስራ የሚከወነው በትምህርት ቢሮዎች ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የማሳተም ስራ ደግሞ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑ ይታወቃል፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments