top of page

መስከረም 14፣2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ከእድሜው እኩል አብሮ ለዘመን የተሻገረውን የኮፐር መስመሮችን ጡረታ ላስወጣ ነው አለ

ኩባንያው በአለሚቱ ከፍተኛ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን የኮፐር መስመር ወደ ፋይበር ለመተካት ወገቡን መታጠቁን ተናግሯል።


#ኢትዮ_ቴሌኮም እንደግዜው የቀድሞውን በማሳረፍ ወደ ዘመናዊ ባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔትና በዳታ ላይ የተመሰረተ የድምጽ (VoIP) አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል የፋይበር ንጣፍ እንደሚጀመር አስረድቷል።


ይህ ፕሮጀክት ወደ ስራ ሲተረጎም ኩባንያው ከደንበኞችን ስባሪ ሳንቲም እንደማይጠይቅ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።


ቀድሞ የተዘረጋው የኮፐር መስመር #ፋይበርን በመተካት ሲነጠፍ ፤ ደንበኞች እንደፍላጎታቸው በሰከንድ እስከ 50 ጊ.ባ የሆነ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ለመስጠት ያስችላቸዋል ተብሏል።


በመጀመሪያው ምዕራፍ በአዲስ አበባ 60,000 በክልል ከተሞች ደግሞ 40,000 በድምሩ 100,000 ደንበኞች ይህን አገልግሎት እንደሚያገኙ ሰምተናል።

#የኮፐር_መስመር በተደጋጋሚ የብልሽትትና ከፍተኛ ሀይል የመጠቀም ባህሪ አለው።


በምትኩ ፋይበር ጥራት ያለው አገልግሎት ከማቅረብ ባለፈ ለደንበኞች ከፍተኛ ፍጥነት የሚፈልጉ (Ultra-low latency) አስተማማኝ የስማርት ሆም፣ ጤና፣ ኢንተርቴይመንት፣ ቪዲዮ ኮንፍራንስ የመሳሰሉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል።


ይህ ግዙፍ ብሔራዊ ፕሮጀክት ግለሰቦች እና ተቋማትን በፈጣን እና ዘመናዊ የፋይበር ኔትወርክ በማስተሳሰር ዘመን የደረሰበትን የቴሌኮም እና ዲጂታል መፍትሄዎችን ያቀብላል ተብሏል።


ኩባንያው ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ሲያስማማ፤ ደንበኞች አገልግሎቱ ብሔራዊና የተሻለ እንደሆነ በመረዳት ትብብር እንዲያደርጉ ኩባንያው መልዕክት ነግሯል።


ይህ የፋይበር ንጣፍ በብሔራዊ ደረጃ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህም ኢትዮ ቴሌኮም ወገቡን እንደታጠቀ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።


ተህቦ ንጉሴ

Commentaires


bottom of page