top of page

መስከረም 2፣2017 - የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 5 ጀምሮ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ እጀምራለሁ አለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊታችን ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሱዳን የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ዕለታዊ በረራ እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡


ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መጀመሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት ያላትን የመዳረሻ ቁጥር ያሳድጋል፤ የንግድና ቱሪዝም ትስስርን በማጎልበት የቀጣናውን የኢኮኖሚ እድገት ያቀለጥፈዋል ብሏል የአየር መንገዱ፡፡

በተያያዘም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኬኒያ ናይሮቢ የሚገኘው የጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሠራተኞች በስራ ማቆም አድማ ላይ በመሆናቸው ምክንያት፤ ወደ ናይሮቢ የሚያደርገው በረራ መቋረጡን ጠቅሷል፡፡


ወደ ናይሮቢ የማደርገው በረራ በታቀደለት መርኃ ግብር እየተከናወነ አለመሆኑን እወቁልኝ ብሏል።


አየር መንገዱ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልፆ በክስተቱ ለተፈጠረው መስተጓጎል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።


ደንበኞች የበለጠ መረጃ ለማግኘት የዓለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል ስልክ ቁጥር ወይም በ 6787 በመደወል አልያም ናይሮቢ የሚገኘውን ትኬት ሽያጭ ቢሮ በአካል በመገኘት ማግኘት እንደሚቻል አየር መንገዱ ተናግሯል።

Comments


bottom of page