በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ተፈናቃዮች በተለይም በአማራ ክልል ያሉት በቂ ባይሆንም መንግስት የሚያቀርበውን እርዳታ እንኳን ማግኘት ስላልቻሉ የረሃብ አዝማሚያ እየታየ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
የመፈናቀል መንስኤዎችን ለይቶ በማክሰም እና የሃገር ውስጥ መፈናቀልን በመከላከል ይሰራል የተባለ ተቋም ሊቋቋም ነው፡፡
የተፈናቃዮችን ጉዳይ ይከታተላል ፣ ሰብአዊ መብታቸውም እንዲከበር ይሰራ የተባለው ራሱን የቻለ ተቋም እንዲቋቋም የሚደነግገው ረቂቅ ህግም ተሰናድቷል፡፡
ህጉ ፈጥኖ ፀድቆ ስራ ላይ እንዲውልም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት እየጠየቁ ነው፡፡
ትዕግስት ዘሪሁን
Kommentit