አይቴልሞባይል ኢትዮጵያ፤ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶችን መስጠቱን ተናገረ።
ኩባንያውለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር ያበረከታቸው ቁሳቁሶች የተለያዩ የትምህርት እና የንፅህና መጠበቂያዎች መሆናቸውን ለሸገር በላከው መግለጫ ላይ ጠቅሷል፡፡
ኩባንያውይህን ያደረገው ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት አስቦ መሆኑን ተናግሯል፡፡
በርክክቡወቅት የአይቴል ኢትዮጵያ ብራንድ ማኔጀር ሚስተር ኤመን ጃ ህጻናቶችንና እናቶችን መደገፍ ለቤተሰብ ደህንነት ትልቅ ትርጉም ያለው በመሆኑ አይቴል ሞባይል ኩባንያ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ድጋፉን እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
የሙዳይበጎ አድራጎት ማህበር መስራች እና ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ በበኩላቸው አይቴል ሞባይል ኢትዮጵያ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ እንዳይለያቸው አደራ ብለዋል።
በ1992 ዓ.ም ኮተቤ አካባቢ በአጸደ ሕፃናት ትምህርት ቤት ጥቂት ሕፃናትን በማስተማር የበጎ አድራጎት ሥራን አንድ ብሎ የጀመረው ሙዳይ የበጎ አድራጎት ማኅበር ላለፉት 23 ዓመታት እናቶችን እና ሕጻናትን ማዕከል ባደረገ መልኩ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ድጋፉንየሰጠው አይቴል ሞባይል የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ከሚያቀርቡ ታላላቅ የሞባይል አምራች ኩባንያዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አይቴልሞባይል በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ በትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያ ስር የሚመረት ነው፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርንወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments