መስከረም 27፣2017 - ንዝረቱ በአዲስ አበባ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአዲስ አበባ ሳይሆን በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ አካባቢ መሆኑ ተሰማ
- sheger1021fm
- Oct 7, 2024
- 1 min read
ንዝረቱ በአዲስ አበባ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው በአዲስ አበባ ሳይሆን በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ አካባቢ መሆኑ ተሰማ።
መንቀጥቀጡም በሬክተር ስኬል መለኪያ 4.9 ሆኖ መመዝገቡን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ተቋም ተናግሯል።


የመሬት መንቀጥቀጡ ከአዲስ አበባ 165 ኪ.ሜ ርቀት ምሽት 2:10:03 ላይ የተከሰተ ሲሆን ንዝረቱ መሬት ለመሬት ተጉዞ በአዲስ አበባ በተለይ ሰሜን እና ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች መሰማቱን የተቋሙ ዳይሬክተር ኤሌያስ ሌዊ(ዶ/ር) ለኢቢሲ ነግረውታል።
የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጉዳት የማድረስ አቅሙ ዝቅተኛ መሆኑም ተነግሯል።
Comentarios