top of page

መስከረም 28፣2016 - የባህር ማዶ ወሬዎች


እስራኤል 300,000 ተጠባባቂ ወታደሮቿን ጠራቻቸው፡፡


ለወታደሮቹ የዘመቻ ጥሪ የተደረገላቸው ሐማስ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ድንገት ደራሽ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ነው፡፡


አሁንም ድረስ በእስራኤል ጦር እና በሐማስ ታጣቂዎች መካከል ከጋዛ ሰርፅ ውጪ ውጊያ እየተካሄደ ነው ተብሏል፡፡


በእስራኤል በአንድ ጊዜ 300,000 ተጠባባቂ ወታደሮች ለግዳጅ ሲጠሩ የአሁኑ የመጀመሪያው እንደሆነ TRT ዎርልድ ፅፏል፡፡


የዘመቻ ጥሪ የደረሳቸው የእስራኤል ወታደሮች ብዛት የግጭቱን ታላቅነት ያሳያል ተብሏል፡፡


እስራኤል መልሶ ማጥቃቷን ልታብሰው እንደምትችልም ግምት አሳድሯል፡፡


አፍሪካ ህብረት በሶማሊያ ያሰማራው ሰራዊት /አትሚስ/ ደረጃ በደረጃ የመውጫው ጊዜ እንዲዘገይ የቀረበውን ጥያቄ ደገፈው፡፡

አትሚስ በቅርቡ 3 ሺህ ወታደሮችን ማስወጣት ይጠበቅበት ነበር፡፡


ይሁንና የሶማሊያ መንግስት የተቀናሽ የአትሚስ ወታደሮች መውጫ እንዲዘገይለት ጥያቄ ማቅረቡን አናዶሉ አስታውሷል፡፡


አትሚስ ቀደም ሲል ሁለት ሺህ ወታደሮችን አስወጥቷል፡፡


የሶማሊያ መንግስት በአትሚስ በመደገፍ በአልሸባብ ፅንፈኛ ቡድን ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከከፈተ ከአመት በላይ ሆኖታል፡፡


ሆኖም ፅንፈኛው ቡድን የደፈጣ፣ ድንገት ደራሽ እና የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃቶችን ማድረስ መቀጠሉን ዘገባው አስታውሷል፡፡



በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራኑ አምባሳደር አገራችን በወቅታዊው የእስራኤል እና የሐማስ ግጭት በጭራሽ እጇ የለበትም አሉ፡፡


እስራኤል ሐማስ ላደረሰባት መጠነ ሰፊ ጥቃት ከኢራን ራስ አልወርድም ማለቷን ጄሩሳሌም ፖስት ፅፏል፡፡


እንደ ሳውዲ አረቢያ ፣ ግብፅ እና ቱርክ ያሉ አገሮች ግጭቱ እንዲቆም እየተማፀኑ ነው፡፡


ከጋዛ ድንበር ሰርገው ወደ እስራኤል የዘለቁት የሐማስ እና የእስላማዊ ጂሃድ ታጣቂዎች እስራኤል ውስጥ ከገደሏቸው በተጨማሪ 120 ያህሉን አግተው ወደ ጋዛ ማምጣታቸው ተሰምቷል፡፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በእስራኤል የአፀፋ ምላሽ እንዳይጎዱ ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች ከግዛቲቱ ለቅቀው እንዲወጡ መጠየቃቸውን አረብ ኒውስ ፅፏል፡፡


አሜሪካ ታላቅ የጦር መርከቧን ወደ ቀጠናው አስጠግታለች ተብሏል፡፡


እስራኤል ወደ ጋዛ የምትልከውን ኤሌክትሪክ አቋርጣለች፡፡


የነዳጅ ዘይት እንዳያፍም አድርጋለች ተብሏል፡፡

የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz

Comments


bottom of page