top of page

መስከረም 28፣2017 - በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር  ካሳ እና 100 ሄክታር  ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

  • sheger1021fm
  • Oct 8, 2024
  • 1 min read

በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ለሚነሱ የግል ባይዞታዎች 5 ቢሊዮን ብር  ካሳ እና 100 ሄክታር  ምትክ መሬት መዘጋጀቱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።


በዚህኛው ምዕራፍ ከሚነሱት ውስጥ 80 በመቶው የቀበሌ ቤት፣ 10 በመቶው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቶች ነዋሪዎች እና 10 በመቶው የግል ባለይዞታዎች መሆናቸውን ከንቲባዋ በሰጡት መግለጫ  ተናግረዋል።


የቀበሌ እና የፌደራል ቤቶች ውስጥ ለነበሩ  4,000 መኖሪያ ቤቶች  መዘጋጀታቸውንም ሰምተናል፡፡

ለስራ እድል ፈጠራ በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ አካላት በቂ የማምረቻ፣ መሸጫ እና ምርት መያዣ ሼዶች በቀበሌ እና በንግድ በቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች ተደራጅተው የንግድ ቦታ እንዲገነቡ  እንዲሁም በአነስተኛ ሱቆች ሲሰሩ ለነበሩ 500  የሱቅ ኮንቴነሮች መዘጋጀታቸውንም ከንቲባዋ ተናግረዋል።


በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት በስምንት ኮሪደሮች 132 ኪሎሜትር ርዝመት እና ከ 2,817 ሄክታር  ቦታ ለማልማት ተቅዷል ተብሏል።


የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት ጥናት መጠናቀቁን ፣ የዲዛይን እና ህዝብን የማወያየት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page