top of page

መስከረም 29፣2017 - የአውቶብስ ትኬት በመቁረጥ ላይ የነበሩ ሶስት ሴቶች አና ጧፍ ስትሸጥ የነበረች አንዲት ሴት በገልባጭ መከና ተገጭተው ህይወታቸው አለፈ

  • sheger1021fm
  • Oct 10, 2024
  • 1 min read

የአውቶብስ ትኬት በመቁረጥ ላይ የነበሩ ሶስት ሴቶች አና ጧፍ ስትሸጥ የነበረች አንዲት ሴት በገልባጭ መከና ተገጭተው ህይወታቸው አለፈ፡፡


ለአራቱ ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነው አደጋ የደረሰው በአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡


አደጋው በመስከረም 28፣2017 ጠዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ ከጎሮ ወደ ኮዬ ሲጓዝ የነበረ ገልባጭ  ተሽከሪካሪ የአውቶብስ ትኬት በመቁረጥ ላይ የነበሩ ሶስት ሴቶቸ እና ጧፍ ስትሸጥ የነበረችን አንዲት ሴት   በመግጨቱ የተከሰተ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተናግሯል፡፡

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪ አሽከርካሪውን ጨምሮ 7 ሰዎች ላይ ከባደና ቀላል ጉዳት ድርሶባቸው ወደ ጥሩንሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ተወስደዋሉ ሲሉ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ነግረውታል፡፡


ሕይወታቸው ያለፈው  ሁሉም ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ20 እስከ 52 ተገምቷል፡፡



Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page