top of page

መስከረም 30፣2016 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ወደ ቴሌ ብር ገንዘብ ስትልኩ የአገልግሎት ክፍያ መቁረጤ ስህተት ነው አለ

  • sheger1021fm
  • Oct 12, 2023
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ወደ ቴሌ ብር ገንዘብ ስትልኩ የአገልግሎት ክፍያ መቁረጤ ስህተት ነው፣ የወሰድኩትንም ገንዘብ እመልሳለሁ አለ።


ባንኩ ሰሞኑን ከንግድ ባንክ ወደ ቴሌ ብር ገንዘብ ሲዘዋወር የቆረጠው ገንዘብ በቴክኒክ ስህተት እንደሆነ ለሸገር ነግሯል።


እንዲህ ያለው ስህተት እንዴት ሊያጋጥም ቻለ ብለን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጠይቀናል።


በንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝደንት ዳህላክ ይገዙ ስህተቱ የተፈጠረው ከሌሎች ሸሪክ ኩባንያዎች ጋር የኮሚሽን ጉዳይ መተግበሪያውን ለመውሰድ ወደ ሥራ ስናስገባ የተፈጠረ ድንገተኛ ገጠመኝ ነው ብለዋል።

ከንግድ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ በዲጂታል ሜዳው ገንዘብ ሲዘዋወር የምትቆርጡት የኮሚሽን መጠን አለ  ወይ ? ይህንንስ ለደንበኞች ለምን አላስረዳችሁም ብለን ሀላፊውን ጠይቀናል።


ዘጠና በመቶ የሚሆነው የገንዘብ ዝውውር ካላአንዳች የኮሚሽን ክፍያ የሚገላበጥ መሆኑንን አቶ ዳህላክ አስረድተውናል።


ይህ ማለት የንግድ ባንክ ደንበኛ ወደ ሌላ የንግድ ባንክ ደንበኛ በሚያስተላልፈው ገንዘብ ኮሚሽን የሚወሰደው  የሚዘዋወረው ገንዘብ ከ10 ሺ ብር በላይ ሲሆን ብቻ ነው ተብሏል።


ሐገር በዲጂታል መንገድ ላይ በመሆኗ ገና ከማለዳው ደንበኞችም ከዚህ ጎዳና እንዳይርቁ፣ እንዳይከፉ ፣የኮሚሽን ክፍያው ምን ያህል ተጠንቷል ብለን የዲጂታል ባንኪንግ ም/ ፕሬዝዳንቱን ጠይቀናቸዋል።


እሳቸው በዲጂታል በታገዘ የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር ወጪ ስላለው እንዲሁም በየጊዜው ማሻሻያ ስለሚደረግበት ይህን ለመሸፈን የአገልግሎት ክፍያውን ለመቀበል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሳሳይ ከዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት እና ከሚቀበለው ኮሚሽን ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያውን በአጭር ጊዜ ታውቁታላችሁም ተብሏል።


ቴክኖሎጂው ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት አድርጌያለሁ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኛን ለማስተናገድ ወጪና ማሻሻያ ይኖራል ማለቱን ተናግሯል።


ዝርዝርዝ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትንና የኮሚሽን ክፍያን በተመለከተ ዛሬ ምሽቱን አልያም ነገ ለደንበኞች ይፋ አደርጋለሁ ብሏል።


ንግድ ባንክ የተፈጠረውን ስህተት እንደሚያርም ፣ለደንበኞቹም አስፈላጊውን መረጃ እንደሚሰጥ  የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ዳህላክ ይገዙ ለሸገር ነግረዋል።


ተህቦ ንጉሴ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page