ከሰሞኑ ይፋ ለተደረገው የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ከአምናውና ከካቻአምናው የተሻለ ቁጥር ያላቸው 5.4 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡
ከ95 በመቶ በላይ ተማሪዎች የመውደቃቸው ነገር የትምህርት ጥራቱ ያለውን ስር የሰደደ የጥራት ችግር ማሳያ ተደርጎ ይጠቀሳል፡፡
የትምህርት ባለሞያዎች በነበረው አሰራር ከቀጠልን ችግሩን መፍታት አንችልም ይላሉ፡፡
የት/ቤት ቁጥር መጨመር እና ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የት/ት ሥርዓቱን መቀየር ብቻውን የትምህርት ጥራቱን ችግር ስለማይፈታው ተያያዥ መፍትሄዎችን አብሮ ማጤን ያስፈልጋል እያሉ ነው፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments