top of page

መስከረም 7፣2017 - በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚዎች ላይ ቀድሞ ይከፍሉት ከነበረው በኪሎ ዋት የ95 ብር ከ87 ሳንቲም ጭማሪ መደረጉ ተረጋገጠ

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በከፍተኛ ኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚዎች ላይ ቀድሞ ይከፍሉት ከነበረው በኪሎ ዋት የ95 ብር ከ87 ሳንቲም ጭማሪ መደረጉ ተረጋገጠ፡፡


የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ ደግሞ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተደረገው ጭማሪ 26 ብር ከ34 ሳንቲም መሆኑን ሰምተናል፡፡


ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በስራ ላይ በቆየው ታሪፍ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በኪሎ ዋት 157 ብር ከ16 ሳንቲም ይከፍሉ ነበር፡፡


በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተደረገው ጭማሪ መሰረት ደግሞ በኪሎ ዋት 183 ብር ከ51 ሳንቲም እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡


ይህም በኪሎ ዋት ከ26 ብር በላይ ጭማሪ እንዲከፍሉ ያደረገ መሆኑን ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የተሳሳተ ዘገባ በመሆኑ ይታረምልኝ ባለው ትናንት በሰራነው ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዘገባ በኪሎ ዋት ከ95 ብር በላይ ጭማሪ መደረጉን አምኖ ይህ ጭማሪ ግን ከፍተኛ የሀይል ተጠቃሚ ለሆኑ ፋብሪካዎች ነው ብሏል፡፡


በየሩብ ዓመቱ የታሪፍ ጭማሪ ይደረጋል የተባለ ሲሆን በ4 ዓመት ውስጥ 40 በመቶ ጭማሪ ይደረጋል ተብሏል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


bottom of page