መጋቢት 10 2017 - ኢድ ኤክስፖ ተከፈተ
- sheger1021fm
- Mar 19
- 1 min read
ኢድ ኤክስፖ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፈተ፡፡
ኤክስፖው እስከ መጋቢት 21 ቀን 2017 ለ13 ቀናት ይቆያል ተብሏል፡፡
#ኢድ_ኤክስፖን 3ኢ ኤቨንትስ ከቢላሉል ሃበሺ የልማት እና መረዳጃ ዕድር ጋር በመተባበር አንዳዘጋጁት ሰምተናል፡፡
ኢድ ኤክስፖ የመገበያያ ኤክስፖ ከመሆኑም በተጨማሪ ኢስላማዊ ቅርሶች የሚጎበኙበት እና የተለያዩ በጎ አድራጎቶች የሚደረጉበት መሆኑ ተነግሯል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ከ150 በላይ የንግድ ኩባንያዎችን ቦታ መያዛቸውን ሰምተናል፡፡
አልባሳት፣ የቤት እቃዎች፣ የተለያዩ ምግቦች አና ሌሎች ምርቶችን የያዙ ነጋዴዎች ይስተፉበታል ተብሏል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments