ሕብረት ኢንሹራንስ ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መስራች ባለድርሻ የሚያደርገውን የ30 ሚሊዮን ብር ድርሻ ገዛ፡፡
የድርሻ ግዢ ሰምምነቱን የሕብረት ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መሰረት በዛብህ እና የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል ፈርመውታል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አንዲቋቋም በየአመታዊ ሪፖርቶቹ ሲጠይቅ፣በመድረኩ ሁሉ ሃሳብ ከማቅረብ ባሻገር ለፖሊሲ እና ለህግ አውጪ አካላት የማማከር ስራ ሲሰራ እንደነበር ዋና አስፈጻሚዋ ወ/ሮ መሰረት በዛብህ ተናረዋል፡፡
የገባያውን መቋቋም በጣም ስንጠብቀው፣ስንፈልገው ነበር ያሉት ዋና አስፈጻሚዋ አሁን ጊዜው ደርሶ ኩባንያው መስራች አባል የሚያደርገውን ደርሻ በመግዛቱ በጣም ድሰተኛ ነን ብለዋል፡፡
የኢንሹራንስ ኩባንያው ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የመስራች ባለአከሲዮንነት ድርሻ ለመግዛት የወሰነውም በጥናት ላይ ተመስርቶ መሆኑን ወ/ሮ መሰረት አስረድተዋል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ እንዲያድግ፣ትልቅ አንዲሆን አብሮ አንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን እስማኤል በበኩላቸው ገበያውን ለመቋቋም የዝግጅት ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት ካማከሯቸው ኩባንያዎች መካከል አንዱ ሕብረት ኢንሹራንስ አንደነበር አንስተዋል፡፡
የኢንሹራንስ ዘርፍ በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ውስጥ መግባቱም በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
ምንም አንኳን አንደ ሀገር የአቅም ውስንነት ቢኖርም ገበያው ሲቋቋም መንግስት ለዚህ የሚሆን ሀብት ሙሉ ለሙሉ ለመመደብ ችግር አልነበረበትም ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው የግሉን ዘርፍ ለማካታት በሚል ክፍት መደርጉን አንሰትዋል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ ከገበያው ድርሻ መግዛቱ የተሻለ፣ቀልጠፋ የፋይናንስ እንቅስቃሴ አንዲኖረው ያስችላል ብለዋል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ የመስራችነት ድርሻን መያዙ አስደስቶናል ያሉት የገባያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ጥላሁን አስማኤል ኩባኝያው የ 30 ሚሊዮን ብር ድርሻ መግዛቱ ለኩባንያው፣ለ ባለአክሲዮኞቹ አንዲሁም ለሰራተኞች አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሳዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መስራች ባለድርሻ የሚያደርገውን የ30 ሚሊዮን ብር ድርሻ የገዛው ሕብረት ኢንሹራንስ የመድን ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል ቀዳሚ ከሆኑት የግል የመድን ኩባንያዎች አንዱ ሲሆን ከተመሰረተም 29 ዓመት ሆኖታል፡፡
የኩባንያው አጠቃላይ የሃብት መጠን ከ 4 ቢሊዮን ብር ባለይ የደረሰ ሲሆን የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ 1.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡
ባለፈው የበጀት ዓመት ኩባንያው የተጣራ 327ሚሊዮን ትርፍ አግኝቻለሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ በቅርቡ ስራ ይጀምራ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማሰባሰብና ሌሎች ዘመናዊ የግብይቶችን ለማካሄድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲባል ሰምተናል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments