top of page

መጋቢት 13፣2016 - ''እንደ አክሱምና ላሊበላ ባሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የመግቢያ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል'' የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር

በተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የሚታየዉ የዋጋ ጭማሪ ጊዜዉን ያገናዘበ አይደለም ተባለ፡፡


ይህንን ያለው የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር ነዉ፡፡


ማህበሩ እንደ አክሱምና ላሊበላ ባሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ጎብኚዎች የሚከፍሉትን የመግቢያ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል ብሏል፡፡


ይህ ደግሞ ጊዜውን የጠበቀ ጭማሪ አይደለም ሲል እየተቃወመዉ ነዉ፡፡


የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበር የቦርድ አባል እና የሞንፔይ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት የሆኑቱን አቶ ያሬድ ሙሉጌታ ለሸገር እንደተናገሩት በዚህ ሰዓት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ያለበት የጎብኚን ቁጥር ማሳደግ ላይ ነው ይላሉ፡፡


ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰራ ያለው ከዚህ ተቃራኒ ነው ያሉ ሲሆን እንደ ላሊበላ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ለመግቢያ ያስከፍሉት የነበረዉ 50 ዶላር፤ አሁን ላይ ይህ ዋጋ እጥፍ ሆኖ ወደ 100 ዶላር አድጓል በማለት ነግረውናል፡፡


ዋጋ ጭማሪዉ የቱሪዝም ዘርፉ ከተቀዛቀዘበት እንዳይወጣ ሊያደርግ ስለሚችል ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባልም ብለዋል፡፡


የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪዝም ልማት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ አዳም በክልሉ ውስጥ ባሉ አንዳንድ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች የዋጋ ጭማሪዎች እየታየ መሆኑን ታዝበናል ይላሉ፡፡


በአማራ ክልል አብዛኛዉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ባለቤትነት የሀይማኖት ተቋማት ነዉ ያሉ ሲሆን የዋጋ ጭማሪ የታየውም በነዚህ ስፍራዎች ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


መንግስት የሚያስተዳድራቸዉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ አልታየባቸዉም ብለዋል፡፡



የኢትዮጵያ አስጎብኚ ማህበራት፤ የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ በተለያዩ ሀገራት የሚዘጋጁ የቱሪዝም አዉደርዕዮች ላይ እየተሳተፍኩ ነው ያለ ሲሆን አላማውም ነገሮች ሲስተካከሉ ጎብኚዎች የሀገሪቱ ቱሪዝም መጥተዉ እንዲጎበኙ ለማስተዋወቅ ነው ብለዋል አቶ ያሬድ፡፡


በረከት አካሉ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




コメント


bottom of page