ሴቶች በኪነ ጥበብ እና በፈጠራ ስራዎች ላይ ያላቸውን ሚና እና ውክልናን በተመለከተ ለፖሊሲ አጥኒዎች ግብዓት ይሆናሉ የተባሉ ጥናቶች ሊደረጉ ነው ተባለ፡፡
ይደረጋሉ የተባሉ ጥናቶች ኢትዮጵያን ጨምሮ በ7 የአፍሪካ ሀገራት፤ ሴቶች በኪነ ጥበቡ ዘርፍ ያላቸውን ውክልና የሚዳስስ እንደሆነም ተነግሯል፡፡
ሴቶች፤ በሙዚቃ፣ በፊልም፣ በፋሽን ኢንዱስትሪ፣ በስዕል፣ በስነ ፁሑፍ እና በመሰል ኪነጥበባዊ ስራዎች ላይ ሴቶች ያላቸውን ዉክልና በጥናቶቹ እንደሚጠኑ ተጠቅሷል፡፡
የ3 ዓመት የጊዜ ገደብ ተቀምጦለታል በተባለው ይህ ጥናት በዘርፉ ሴቶች የሚገጥሟቸው ዕድሎች እንዲሁም ፈተናዎችንም እንደሚለይ ታልሞለታል ተብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments