top of page

መጋቢት 14፣2016 - ዛሬ ማለዳ በእንጦጦ ጋራ ስር የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሞ ነበር ተባለ

  • sheger1021fm
  • Mar 23, 2024
  • 1 min read

ከጥዋቱ 1 ሰዓት ከ45 ደቂቃ 25 ሰኮንድ የቆየ የመሬት መንቀጥቀጥ በእንጦጦ ጋራ ስር ማጋጠሙን ሰምተናል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በርዕደ መርት መለኪያ(በሬክትር ልኬት )2.0 ሆኖ መመዝገቡን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  የስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም ሀላፊ ፕሮፈሰር አታላይ አየለ ለሸገር ነግረዋል።


ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ እና ፉሪ ተራራ ሥር በሚገኙ መሣሪያዎች የተመዘገበ መሆኑ ተነግሯል።


የመሬት መንቀጥቀጡ የተፈጠረው 9.1113 ኬክሮስና 38.753 ኬንትሮስ መስመሮች በሚገናኙበት ነጥብ ላይ ያረፈ ሲሆን ይህም በእንጦጦ ጋር ስር መሆኑን ማወቅ ተችሏል ተብሏል።


በሰሜን አዲስ አበባ በተለይም ፎቅ ላይ ያሉ ነዋሪዎች ንዝረቱን መስማታቸውን አስረድተዋል።


የመሬት መንቀጥቀጡ ጉዳት የማድረስ አቅሙ በጣም ዝቅተኛ መሆኑንም ፕሮፈሰር አታላይ ነግረውናል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page