የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በአለም አቀፍ ንግድ ላይ የተሠማሩ አባላቱ የሚገጥማቸውን ችግር ያቃልላል ያለውን የዲጂታል ስርዓት ይፋ አደረገ።
የዲጂታል ስርዓቱ በአለም አቀፍ ንግድ ለተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የገበያ መዳረሻዎችን እና ህጎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የሚሰጥ መሆኑ ተጠቅሷል።
የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት 17 ሺህ አባላት አንዳሉት የተናገሩት የምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም፤ ከእነዚህ መካከል ከ10 ሺህ የሚበልጡት በአለም አቀፍ ንግድ የተሰማሩ ናቸው ብለዋል።
ከእነዚህ ከ10 ሺህ የሚበልጡት የምክር ቤቱ አባላት፤ 76 በመቶዎቹ ላኪዎች እንደሆኑ አቶ ሺበሺ ተናግረዋል።
22.6 በመቶዎቹ ደግሞ አስመጪዎች ናቸው ብለዋል።
በአለም አቀፍ ንግድ የተሠማሩት አነዚህ የምክር ቤቱ አባላት በርከት ያሉ ችግሮች እንደሚገጥሟቸው ዋና ፀሃፊው ተናግረዋል።
ስለ ውጪ ገበያ በቂ ግንዛቤ አለመኖር እና የመረጃ እጥረት ከእነዚህ መካከል እንደሆኑ ጠቅሰዋል።
ችግሮቹን ለመፍታት የዲጂታል ፖርታል ከGIZ ጋር በመተባበር ምክር ቤቱ አዘጋጅቷል ብለዋል ።
በዚህም በአለም አቀፍ ንግድ ላይ የተሠማሩ የምክር ቤት አባላት በውጪ ስላሉ የገበያ ዕድሎች በቀላሉ ማወቅ እንደሚችሉ ተጠቅሷል።
ስለ ገዥ ሀገራት ህጎችና የጥራት መስፈርቶችም እንዲሁ መረጃ ይኖራቸዋል ተብሏል።
ምክር ቤቱ በአለም አቀፍ ንግድ የተሰማሩ አባላቱን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ተጨማሪ ስራዎችን ወደፊትም እንደሚሰራ ዛሬ ከሰአት በኋላ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ሲናገር ተገኝተን ሠምተናል፡፡
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios