መጋቢት 17 2017 - ብሔራዊ ባንክ በኢኮኖሚ ውስጥ የተጠናከረው ለውጥ አለ ቢልም እኛ የጠየቅናቸው ባለሞያ በዚህ አይስማሙም
- sheger1021fm
- 7 days ago
- 1 min read
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ በዳግም ስብሰባው የገንዘብ አቅርቦት፣ የፋይናንስ ዘርፍ እንቅስቃሴዎችን፣ የገንዘብ ዝውውር፣ የፊስካል፣ የዋጋ ግሽበት እና አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታውን ገምግሟል።
አሁን ያለውን 15 በመቶ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በመጪዎቹ ወራቶች ቅናሽ እንዲያሳይ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድን መከተል አስፈላጊ መሆኑንን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ተናግሯል፡፡
ለዚህም ሲባል #የብሔራዊ_ባንክ የፖሊሲ ተመን አሁን ባለበት እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡
ማዕከላዊ ባንኩ የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መምጣቱን ተናግሮ በየካቲት ወር መጨረሻም 15 በመቶ ደርሷል ብሏል።
ባንኩ የገንዘብ ሁኔታን ገምግሜያለሁ ካለ በኋላ የገንዘብ ዝውውሩ በኢኮኖሚ ውስጥ የተጠናከረ እድገት አሳይቷል ይላል።

በዚህ መግለጫ ማዕከላዊ ባንኩ ስለ ውጭ ምንዛሪ አስተዳደር በተለይ በመደበኛው እና በትይይዩ ገበያ ያለውን ልዩነት በዝርዝር አላስረዳም።
ብሔራዊ ባንክ በኢኮኖሚ ውስጥ የተጠናከረው ለውጥ አለ ቢልም እኛ የጠየቅናቸው ባለሞያ በዚህ አይስማሙም።
አብዱልመናን መሀመድ(ዶ/ር) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚና ፋይናንስ የ ፒኤችዲ ወረቀት ፅፈዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://0fj.cc/gcZ9SquRbdr
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments