top of page

መጋቢት 18፣2016 - ሸቀጦች እና ምርቶችም በሚፈለገው መጠን ወደ ክልሉ እየገቡ ባለመሆኑ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ ሆኗል ተብሏል

ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚያስገቡ መንገዶች በፀጥታ ስጋት በመዘጋታቸው በክልሉ ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞች የሚደረገው ድጋፍ በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጎታል ተባለ፡፡


ሸቀጦች እና ምርቶችም በሚፈለገው መጠን ወደ ክልሉ እየገቡ ባለመሆኑ የኑሮ ውድነቱ እንዲባባስ ሆኗል ተብሏል፡፡


ክልሉ ከኦሮሚያ እና አማራ ክልል እንዲሁም ከሱዳን ጋር የሚዋሰን እንደመሆኑ በሶስቱም በኩል ያለው የፀጥታ ችግር በክልሉ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የእርዳታ ድጋፍ ማግኘት እንዳልቻሉ ሰምተናል፡፡


ከዚህ ቀደምም በከፍተኛ ግጭት ውስጥ የነበሩ የቤንሻንጉል ክልል ወደ አጎራባችም ይሁን ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዝግ እንደሆነበት ለሸገር ነግረዋል፡፡


ይህም ትልቅ መስተጓጎልና ከፍተኛ የሆነው የኑሮ ውድነት እንደፈጠረባቸው ተነግሯል፡፡


ማርታ በቀለ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page