top of page

መጋቢት 18፣2016 - በኢትዮጵያ ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶ የሚሆነው በአሲዳማ አፈር የተጠቃ ነው ተባለ

  • sheger1021fm
  • Mar 27, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታረሰው መሬት 43 ከመቶ የሚሆነው በአሲዳማ አፈር የተጠቃ ነው ተባለ።


የግብርና ሚኒስቴር ሀገሪቱ ውስጥ ከሚታረሰው መሬት 7 ሚሊዮን ሄክታር የሚሆነው የአሲዳማ አፈር ተጠቂ ነው ብሏል።

ከዚህ ውስጥ 3.1 ሚሊዮን ሄክታሩ በከፍተኛ ሁኔታ በአሲድ መጠቃቱ ተነግሯል።


መሬቱን ለግብርና ስራ ለማዋል በዓመት 6.2 ሚልየን ኩንታል ማዳበሪያ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን 70 ከመቶ የሚሆነው የአፈር ማዳበሪያ ይባክናል ተብሏል።


በዚህም ሀገሪቱ 19 ቢልየን ብር በአፈር አሲድ ምክንያት በአመት ይባክንባታል ሲል የግብርና ሚንስቴር ተናግሯል።

የግብርና ሚንስቴር ሚንስትር ግርማ አመንቴ በአሲዳማ አፈር ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ምርት ይባክንባታል ሲሉም አስረድተዋል።


አሲዳማ አፈር በአብዛኛው የሚከሰተው በደጋ እና ወይና ደጋ የኢትዮጵያ ክፍል አካባቢ ነው ያሉት ሚንስትሩ ለዚህም ምክንያቱ መሬቱ፤ በዝናብ ስለሚታጠብና በአንዳንድ የአፈር ማዳበርያ አጠቃቀም ተብሏል፡፡



አሲዳማ አፈር ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል የሚሉት ሚንስትሩ መሬቱን ለማከም ኖራ እየተጠቀምን ነው ብለዋል።


ኖራ ለማምረት ኢትዮጵያ በቂ ማዕድን እንዳላት የማዕድን ሚኒስቴር አረጋግጧል ያሉት ሚኒስትሩ በ2016/17 የምርት ዘመን ከ105 ሺህ ሄክታር በላይ አሲዳማ መሬት ለማከም ታቅዷል ብለዋል።


የግብርና ሚኒስቴር አሁን ላይ በሰርቶ ማሳያ ለመስራት ያቀደው የአሲድ አፈር ማከም ስራ በሚቀጥሉት ጊዜያት በስፋት ለመስራት አቅዷል ተብሏል።


ከዚህ በፊት 103 ሺህ ሄክታር አሲዳማ መሬት በግብርና ኖራ የማከም ስራ ተሰርቶ ምርታማነት እስከ 100 በመቶ ጨምሯል መባሉን ሰምተናል።


ለዚህም 2.8 ቢልዮን ብር ተመድቧል የተባለ ሲሆን 50 ከመቶ የሚሆነው መንግስት ቀሪው ገበሬው ይሸፍናል ተብሏል።


አሁን ላይ ኢትዮጵያ በዓመት 1.1 ሚሊዮን ቶን የግብርና ኖራ በ20 የሲሚንቶና የኖራ አምራች ኢንዱስትሪዎች ታመርታለች ተብሏል።


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page