top of page

መጋቢት 19፣2016 - ኤም ፔሳ ሳፋሪኮም የደንበኞቹ ብዛት 4.2 ሚሊዮን መድረሱን ተናገረ

የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢው ኤም ፔሳ ሳፋሪኮም የደንበኞቹ ብዛት 4.2 ሚሊዮን መድረሱን ተናገረ።


ኤም ፔሳ ሳፋሪኮም አዲስ ተጠቃሚ እና ግብይታቸውን በፔሳ ሳፋሪኮም ያካሄዱ ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን፣ ወኪሎችን እና ነጋዴዎችን የሸለመበት መርሃ ግብሩን በዛሬው እለት ተጠናቋል።

የሽልማት መርሀ ግብሩ ''ተረክ በ ኤም ፔሳ’’በሚል ባለፊት ሶስት ወራት የቆየ ነው ተብሏል።


በመርሃ ግብሩ አጠቃላይ ለእድለኞች የተሸለሙ 4 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢሎች፣ 24 ባጃጆች፣ 2160 ስልኮች እና በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዋጋ ያላቸው የአየር ሰዓት ሽልማቶችም በስድስት ዙር ለባለእድለኞች ተሸልመዋል።

የሽልማት መርሀ ግብሩ መጨረሻ የሆነው የስድስተኛው ዙር ሽልማት አሰጣጥ እና የመርኃ ግብሩ መዝጊያ ስነ ስርዓት ዛሬ በጊዮን ሆቴል ተካሂዷል።



የመርሀ ግብሩ መጨረሻ በሆነው ስድስተኛ ዙር እድለኞች ከሁለት መኪኖች በተጨማሪ ሦስት ባጃጆች፣ 360 ስልኮች እና በሺህዎች የሚቆጠሩ የአየር ሰዓት እጣዎችን ተሸልመዋል።


የM-PESA ሳፋሪኮም የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ስትራቴጂክ አጋርነት ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ክፍሌ ኃ/እየሱስ መርሐ ግብሩ የእድለኞችን ሕይወት ከመለወጡ በተጨማሪ የገንዘብ ክፍያን እና ዝውውርን ያቀለለ፣ የM-PESA መተግበሪያን ያስተዋወቀ እና የብራንዱን ታዋቂነት ከፍ ያደረገ መርኃ ግብር ነበር ብለዋል።


ተረክ ኤም ፔሳ፤ ደንበኞች ስለ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎት የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር እና አጠቃቀሙን ለማጎልበት ያለመ መርሀ ግብር ነው ተብሏል፡፡


ኤም ፔሳ ሳፋሪኮም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በገኘው የፋይናንስ አገልግሎት አቅራቢነት ፍቃድ በነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎች ማቅረብ ላይ መሆኑን ተናግሯል።



ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


bottom of page